በኢትዮጵያ ሕግ መሰረት ይቅርታ ለማን እና እንዴት ይደረጋል?
ማክሰኞ፣ የካቲት 6 2010ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ መንግሥት በእስር ላይ የሚገኙ ፖለቲከኞች እና ጋዜጠኞችን ክስ ለማቋረጥ፣ የተበየነባቸውን ደግሞ በይቅርታ ለመፍታት መወሰኑ አይዘነጋም። የቀረበባቸው ክስ ከተቋረጠላቸው መካከል ዛሬ ከእስር የተፈቱት አቶ በቀለ ገርባ እና ስድስት የኦሮሞ ፌድራሊስት ኮንግረስ አመራሮች እና አባላት ይገኙበታል። የሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት የይቅርታ ሰነድ እንዲፈርሙ ተጠይቀው ሳይቀበሉት ቀርተዋል። የኮሚቴው አራት አባላት ዛሬም ከእስር አልተፈቱም።
ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እና ፖለቲከኛው አቶ አንዱዓለም አራጌ ጥፋተኛ ተብለው በእስር ላይ ናቸው። የኢትዮጵያ መንግሥት እስክንድር እና አንዱዓለምን ከሚፈታቸው መካከል እንደሆኑ ቢጠቅስም እስከዛሬ አልተፈቱም። ቤተሰቦቻቸው በኢትዮጵያ መንግሥት ሽብርተኛ ተብሎ የተፈረጀው የግንቦት ሰባት አባል ነበርን የሚል ደብዳቤ እንዲፈርሙ መጠየቃቸውን ተናግረዋል። ክስ ማቋረጥ እና ይቅርታ በኢትዮጵያ ሕግ ያላቸው ልዩነታቸው ምንድነው? የሕግ ባለሙያው አቶ ተማም አባቡልጉ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
እሸቴ በቀለ
ሸዋዬ ለገሠ