ክርክር ያስነሳዉ የግብፅ መሪ የጀርመን ጉብኝት
ሐሙስ፣ ግንቦት 13 2007ማስታወቂያ
የጀርመን ታህታህ ምክር ቤት አንደኛ ፕሬዝደንትና አፈ ጉባኤ የሆኑት ኖርበርት ላመርት የፕሬዝደንት ሲሲን ጉብኝት እንደሚቃወሙ እሳቸዉን በእንግድነት መቀበልም ለሰብዓዊመብቶች ጥሰት ጆሮ አለመስጠት መሆኑን የሚዘረዝር ደብዳቤ በበርሊን ለግብፅ ኤምባሲ ማላካቸዉ ተሰምቷል። የግብጽ ፍርድ ቤት የቀድሞዉ የግብፅ ፕሬዝደንት ሞሀመድ ሙርሲና ሌሎች አንድ መቶ እስረኞች ከእስር ቤት ለማምለጥ ሲያሴሩ ተደርሶባቸዋል በሚል የሞት ቅጣት በይኗል። የጀርመኑ ፖለቲከኛ ይህንን አጥብቀዉ ተችተዋል። የሀገሪቱ መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል ግን አል ሲሲን ተቀብለዉ ለማነጋገር ዝግጁነታቸዉን ይፋ አድርገዋል። የአልሲሲ የጀርመን ጉብኝት ሃሳብ በጀርመን ፖለቲከኞች መካከል ያስነሳዉን አለመግባባት በሚመለከት በርሊን የሚገኘዉ ዘጋቢያችን ይልማ ኃይለሚካኤልን ስቱዲዮ ከመግባቴ አስቀድሜ በስልክ አነጋግሬዋለሁ።
ይልማ ኃይለሚካኤል
ሸዋዬ ለገሠ
አርያም ተክሌ