ኬንያ የተገኘው አፅምና ፋይዳው
ዓርብ፣ ጥር 13 2008ማስታወቂያ
ኬንያ ውስጥ የተገኘው ከ10 ሺህ አመት በፊት የተገደሉ የአንድ የጎሳ አባላት ሳይሆን እንዳልቀረ የተገመተ አፅም በጥንት ጊዜ የሚደርሱ እልቂቶችና ግጭቶች ማስረጃ ሆኖ ሊቀርብ እንደሚችል ሳይንቲስቶች አስታወቁ። ሳንቲስቶች እንዳሉት ቱርካና በተባለው ሐይቅ አቅራቢያ በተካሄደ ቁፋሮ የተገኘው በአንድ ላይ የታሰሩ እና ከባድ ጥቃት የደረሰባቸው የ12 ሰዎች እንዲሁም የሌሎች 15 ሰዎች አፅም ምናልባትም ሰዎቹ አዳኞች ሳይሆኑ እንዳልቀረ ይጠቁማል። የአንዳንዶቹ አፅሞች የራስ ቅል ከድንጋይ የተሠራ ጦር እንደተሰካባቸው የተገኙ ሲሆን፤ ሌሎቹ ደግሞ ሰዎቹ ተደብድበው መገደላቸውን የሚያመለክቱ ናቸው። ስለተገኘው አጽምና ስለ ጥናቱ ፋይዳ የናይሮቢውን ወኪላችንን ፋሲል ግርማን በስልክ አነጋግረነዋል።
ፋሲል ግርማ
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ