ኬንያ ለአፍሪቃ ኅብረት ያቀረበችዉ ኃሳብና የኬንያ መኮንኖች ቅሌት
ሰኞ፣ ጥር 23 2008ማስታወቂያ
ፕሬዚዳንቱ ይህን ኃሳብ ያቀረቡት በሶማልያ የኧሸባብ ጽንፈኛ ቡድን ታክቲኩን እየቀያየረ ጥቃት እያደረሰ መሆኑን ተከትሎ እንደሆነ ነዉ የተጠቀሰዉ። በሌላ በኩል በሶማልያ የሰፈረዉ የኬንያ ጦር ባልደረቦች ከኧሸባብ ጋር ግንኙነት እንዳላቸዉና በተለይ ደግሞ ከሰልና ሌሎች ቁሳቁሶችን እንደሚነግዱ በቅርቡ የወጣ አንድ ዘገባ አጋልጦአል። በሶማልያ የሚገኙ የኬንያ የጦር መኮንኖች ቀረጥ ይቀበላሉ ስኳር ይነግዳሉ፤ የሚል ወቀሳም ተያይዞ ይፋ ሆኖዋል። በኬንያ ናይሮቢ የሚገኘዉን የዶይቼ ቬለን ወኪል ፕሬዚዳንት ኡሁሪ ኬንያታ በአፍሪቃ ኅብረት ጉባዔ ላይ አቀረቡት ስለተባለዉ ንድፈ ኃሳብና፤ የኬንያ የጦር መኮንኖችን ቅሌት በተመለከተ በስልክ ጠይቀነዉ ነበር።
ፋሲል ግርማ
አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሃመድ