ካርኒቫል በጀርመን
ሰኞ፣ የካቲት 23 2001ማስታወቂያ
የጀርመኗ መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማን ልብስ የሙጥኝ ብለው በአየር ላይ ሲንሳፈፉ ታይተዋል። ዋነኞቹ የጀርመን የፖለቲካ ፓርቲዎች CDU እና SPDም የቡጢ መድረክ ተዘጋጅቶላቸው ጓንቶቻቸውን አጥልቀው ተፋጠዋል። በሚሊዮን የሚቆጠሩ ታዳሚያንም በምዕራብ ጀርመን የNord Rhein Westfalen ግዛት ውስጥ በሚገኙ ከተሞች ግልብጥ ብለው ተጎዳና ተ ገኝተዋል። ሰዉ የጎዳና ላይ ካርኒቫሉን የፖለቲካ፣ የማኍበራዊና የምጣኔ ሀብታዊ ስላቅ ሲያንጸባርቅበት ታይሮዋል።