1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ከ49 ሺ በላይ ተፈናቃዮች ወደ ነበሩበት ይመለሱ ይሆን?

ሐሙስ፣ ግንቦት 13 2012

ባለፉት ሁለት ዓመታት በተፈጠሩ ግጭቶች ከቤኒሻንጉል ክልል የተፈናቀሉ ከ49 ሺህ በላይ ወገኖችን ወደ ነበሩበት ለመመለስ እየተሰራ እንደሆነ የአማራና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች አመለከቱ፡፡ ከምዕራብና ማዕከላዊ ጎንደር ዞኖችና ከኦሮሚያ ክልል ተፈናቅለው የነበሩ ከ80 ሺህ በላይ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው መመለሳቸውን የአማራ ክልል አሳታውቋል፡፡

https://p.dw.com/p/3ca0r
Lijalem Zelalem,
ምስል DW/A. Mekonnen

የተፈናቃዮች ሁኔታ በአማራ ክልል!

የተፈናቃዮች ሁኔታ በአማራ ክልል!

ባለፉት ሁለት ዓመታት በተፈጠሩ ግጭቶች ከቤኒሻንጉል ክልል የተፈናቀሉ ከ49 ሺህ በላይ ወገኖችን ወደ ነበሩበት ለመመለስ እየተሰራ እንደሆነ የአማራና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች አመለከቱ፡፡ ከምዕራብና ማዕከላዊ ጎንደር ዞኖችና ከኦሮሚያ ክልል ተፈናቅለው የነበሩ ከ80 ሺህ በላይ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው መመለሳቸውን የአማራ ክልል አሳታውቋል፡፡ባለፉት ሁለት ዓመታት በተለያዩ አካባቢዎች በነበሩ ግጭቶች የሰው ሕይወት አልፏል፣ አክል ጎድሏል ንብረትም ወድሟል፡፡ ሌሎቸ  በርካታ የአማራ ክልል ተወላጆች ከቀያቸው ተፈናቅለው በተለያዩ የመጠለያ ካምፖች ተጠልለው ቆይተዋል፡፡በአማራና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች አዋሳኛ አካባቢዎች በተለያዩ ጊዜዎች በተነሱ ግጭቶች ምክንያት 49 ሺህ ተፈናቃዮች በአማራ ክልል 4 አካባቢዎች እንደሚገኙ የአማራ ክልል አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትናና ልዩ ድጋፍ የሚሹ አካባቢዎች ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ዘለዓለም ልጃለም በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አመልክተዋል፡፡ ተፈናቃዮቹን ወደ መጡበት ለመመለስ እየተሰራ እንደሆነም ተናገረዋል፡፡የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአደጋ ስጋትሥራ አመራር ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ታረቀኝ ታሲሳ በበኩላቸው ተፈናቃዮችን ወደነበሩበት ለመመለስ ትኩረት ተስጥቶ እየተሰራ እንደሆነና ያለው ሰላምም አስተማማኝ እንደሆነ ለዶይቼ ቬለ በስልክ ተግረዋል፡፡ከ10 ሺህ በላይ የሚሆኑ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው መመለሳቸውን አስታውሰው  እስከ ግንቦት 30/2012 ዓ ም ሁሉም ተጠቃልለው ወደ ቀደመው ቀያቸው  እንደሚመለሱም አቶ ታረቀኝ አስረድተዋል፡፡ተፈናቃዮች ወደመኖሪያ ቀያቸው እስኪመለሱ ድረስ አስፈላጊው እገዛ እየተደረገላቸው እንደሆነም የአማራ ክልል አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትናና ልዩ ድጋፍ የሚሹ አካባቢዎች ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ዘለዓለም ልጃለም አስረድተዋል፡፡ይህ በእንዲህ እንዳለ ከዚህ በፊት በምዕራብና ማዕከላዊ ጎንደር ዞኖች በነበሩ ግጭትችእንዲሁም  ከኦሮሚያ ክልል ተፈናቅለው የነበሩ ከ80 ሺህ በላይ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው መመለሳቸውን ኮሚሽነር አቶ ዘለዓለም ልጃለም ተናግረዋል፡፡አቶ ዘለዓለም አንዳሉትበ ተለይ ከአማራና ቅማነት ጋር በነበሩ ግጭቶች 7 ሺህ ህል ቤቶች መቃጠላቸውን አመልክተው ከ5 ሺህ በላይ   ቤቶች እንደገና መገንባታቸውን ገልፀዋል፡፡ባለፉት አመታት በአማራ ክልል የነበሩ ተፈናቃዮችን መልሶ ለማቋቋም በተደረገ የሀብት ማሰባሰብ ስራ ከህብረተሰቡ፣ ከድርጅቶች፣ ከግለሰቦች፣ ከባለሀብቱና ከአማራ ክልል መንግስት ወደ 465 ሚሊዮን ብር ማሰባሰብ መቻሉን ኮሚሽነሩ አመልክተዋል፡፡

ዓለምነው መኮንን