የገንዘብ ማሸሽ ቅሌት
ሰኞ፣ ጥቅምት 27 2010ማስታወቂያ
ፓራዳይዝ ፔፐርስ በሚል መጠሪያ ስር በወጡት ሰነዶች መሰረት፣ የገቢ ግብር ላለመክፈል በሚል ገንዘባቸውን ቀረጥ ወደማያስከፍሉዋቸው ሀገራት አሸሽተዋል በሚል ስማቸው ከተጠቀሱት መካከል የእንግሊዝ ንግሥት ኤልሳቤጥ ዳግማዊት፣ የካናዳ ጠቅላይ ሚንስትር ጃስቲን ትሩዶ፣ የዩኤስ አሜሪካ የንግድ ሚንስትር ዊልበር ሮስ፣ ሌሎች የዩኤስ ካቢኔ አባላት ፣ ከአስር የሚበልጡ የፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ አማካሪዎች እና በምርጫ ዘመቻ ገንዘብ የሰጡዋቸው ግለሰቦች፣ እንዲሁም፣ ናይክ፣ አፕል፣ ፌስቡክ እና ኡበርን የመሳሰሉት የንግድ ተቋማት ይገኙባቸዋል።
መክብብ ሸዋ/አርያም ተክሌ
ሂሩት መለሰ