ውዝግቦች
ከዩናትድ ስቴትስ ካናዳ የሚገቡ ስደተኞች
ዓርብ፣ ሚያዝያ 13 2009ማስታወቂያ
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት የዶናልድ ትራምፕ መስተዳድር ሐገሩ ሥለሚገኙ ስደተኞች የሚከተለዉን መርሕ በመሸሽ ከዩናይትድ ስቴትስ ዳግም ወደ ካናዳ የሚፈልሱ ስደተኞች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ነዉ።የካናዳ መንግሥት እንዳስታወቀዉ አራተኛ ወሩን በያዘዉ በጎርጎሪያዉያኑ 2017 ከዩናይትድ ስቴትስ ካናዳ የገቡት ዳግም ተሰዳጆች ቁጥር 1860 ደርሷል።ከነዚሕ ስደተኞች መካከል ከ880 የሚበልጡት ካናዳ የገቡት ባለፈዉ መጋቢት ነዉ።አክመል ነጋሽ ከቶሮንቶ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።
አክመል ነጋሽ
ነጋሽ መሐመድ
አርያም ተክሌ