ከብ/ቡድኗ ድል በኋላ የጀርመን ገጽታ በሌሎች እይታ
ሐሙስ፣ ሐምሌ 10 2006ማስታወቂያ
ድሉ ያስከተለው የደስታ ስሜት በእግር ኳስ አፍቃሪው የጀርመን ሕዝብ ብቻ ሳይሆን በመላይቱ ሀገር አሁንም ገና እንደደመቀ ነው። የመገናኛ ብዙኃንም ብዙ እያሉበት ነው። በውጭውስ ዓለም ያለው አስተያየት ምን ይመስላል? እንደሚታወቀው፣ ጀርመናውያን በሌሎች ሀገራት ከስራ ወዳድነታቸው እና ከከፍተኛ የማደራጀት ችሎታቸው ጎን በብዛት የሚታወቁት ዝግ እና የማይመቹ በመሆናቸውም ነው። እና የጀርመን ብሔራዊ ቡድን በብራዚል የዋንጫ ግጥሚያ ላይ ያሳየው ማራኪ እና ጠንካራ የአጨዋወት ስልት እና ዲሲፕሊን ፣ በሌሎች ሀገራት ውስጥ ስለ ጀርመን ያለውን አመለካከት ምን ያህል ይቀይረዋል? የለንደን፣ ፈረንሳይ እና ዋሽንግተን ወኪሎቻችን በየሚኖሩባቸው ሀገራት ያለውን አስተያየት እንዲነግሩን ጠይቄአቸዋለሁ።
ድልነሳ ጌታነህ፣ ሀይማኖት ጥሩነህ፣ አበበ ፈለቀ፣
አርያም ተክሌ
ሸዋዬ ለገሠ