ከስደተኞች ጋር የተጋጩት የመቂዶንያ ፖሊሶች
ሰኞ፣ ሚያዝያ 3 2008ማስታወቂያ
ትናንት የመቄዶንያ የድንበር ጠባቂ ፖሊሶች ድንበር ላይ ኬላና አጥር አፍርሰዉ ከግሪክ ወደ ምዕራብ አዉሮጳ ለመግባት ሙከራ ባደረጉት ስደተኞች ላይ አስለቃሽ ጢስ ተኩሰዉ ወደኋላ እንዲያፈገፍጉ አድርገዋል። የጀርመን የመገናኛ ብዙኃን በሰፊዉ እንደዘገቡት በትናንቱ ግጭት ወደ 300 ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል። የመቄዶንያ ፖሊስ ርምጃ ተገቢና ተመጣጣኝ ያልሆነ ሲሉ የግሪክ መንግሥትና ሌሎች የአዉሮጳ ሃገራት ድርጊቱን አዉግዘዋል።
ይልማ ኃይለሚካኤል
አዜብ ታደሰ
ሸዋዬ ለገሠ