ከሳሽ ያጡት እነ ኤልያስ ለጠቅላይ ሚኒሥትሩ አቤቱታ አቀረቡ
ሰኞ፣ ሚያዝያ 30 2009ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ መንግሥት ከደነገገው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በኋላ የታሰሩት ኤልያስ እና ዳንኤል እስካሁን በይፋ ክስ አልተመረተባቸውም። በእስር ላይ «ተጉላልተናል» ያሉት ጋዜጠኛ ኤልያስ እና አቶ ዳንኤል ዛሬ ለጠቅላይ ሚኒሥትሩ ለፃፉት የአቤቱታ ደብዳቤ የሚሰጣቸው ምላሽ የታወቀ ነገር የለም። አዲስ አበባ የሚገኘው የዶይቼ ቬለ ወኪል ያነጋገራቸው የተጠርጣሪዎቹ ባልደረባ አቶ ኤልያስ እና አቶ ዳንኤል የጤና እክል እንደገጠማቸው ተገቢውን የሕክምና ክትትልም አለማግኘታቸው ተናግረዋል።
ዮሐንስ ገብረእግዚዓብሔር
እሸቴ በቀለ
አዜብ ታደሰ