ኦፌኮ እና ሰማያዊ ፓርቲ የኦነግ አመራሮች አቀባበል ሰላማዊ እንዲሆን ጠየቁ
ዓርብ፣ መስከረም 4 2011ማስታወቂያ
የኦሮሞ ፌድራሊስት ኮንግረስ እና ሰማያዊ ፓርቲ ነገ ቅዳሜ መስከረም 5 ቀን 2010 ዓ.ም. ለኦሮሞ ነፃነት ግንባር አመራሮች የሚደረገው አቀባበል ሰላማዊ እንዲሆን ጥሪ አቀረቡ። የኦሮሞ ፌድራሊት ኮንግረስ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀ-መንበር አቶ ሙላቱ ገመቹ ሕዝቡ ሊደማመጥ ይገባል ብለዋል። የኦሮሞ ነፃነት ግንባር አመራሮች የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች ናቸው ያሉት የሰማያዊ ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አበበ አካሉ እንግዶቹን ለመቀበል የብሔር እና የቋንቋ ልዩነት ገደብ ሊሆን አይገባም ብለዋል። የአዲስ አበባዉ ዘጋብያችን ተጨማሪ ዘገባ አለው።
ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር
እሸቴ በቀለ
ኂሩት መለሰ