1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

„ኦሎምፒክ“ የአለም የባህል መድረክ

ሐሙስ፣ ሐምሌ 19 2004

ብሪታንያ በመዲናዋ ለንደን ከአለም ዙርያ የመጣን ህዝብ በኦሎምፒክ መንደር ጥላ አሰባስባ፣ በስፖርት ዉድድር አካፍላ፣ ባህልዋን እና ልምድዋን ለማስተዋወቅ ዝግጅትዋን ጨርሳ እነሆ ነገ የኦሎምፒክ ዉድድሩን ለመጀመር በተጠንቅቅ ላይ ትገኛለች። እ,አ 1896 ለመጀመርያ ጊዜ በግሪክ በተካሄደዉ ዉድድር ላይ 11 አገራት ተካፋይ ነበሩ። ኢትዮጵያስ?

https://p.dw.com/p/15esP
Kenenisa Bekele of Ethiopia celebrates with a national flag after winning the men's 10,000-meter during the athletics competitions in the National Stadium at the Beijing 2008 Olympics in Beijing, Sunday, Aug. 17, 2008. (AP Photo/Kevin Frayer)
አትሌት ቀነኒሳ በቀለ እ,ጎ,አ 2008 ቤጂንግ ኦሎምፒክ በ10,000 ሜር ሩቻ ያሸነፈበትምስል AP

ብሪታንያ በመዲናዋ ለንደን ከአለም ዙርያ የመጣን፣ በቋንቋ፣ በባህል፣ በቀለም፣ በሃይማኖት የሚለያይ ህዝብን በኦሎምፒክ መንደር ጥላ አሰባስባ፣ በስፖርት ዉድድር አካፍላ፣ የኦሎምፒክ ተካፋይ አገር ባህል እና ልምድን አዉቃና ባህልዋን እና ልምድዋን ለማስተዋወቅ ዝግጅትዋን ጨርሳ እነሆ ነገ የኦሎምፒክ ዉድድሩን ለመጀመር በተጠንቅቅ ላይ ትገኛለች። ኦሎምፒክ ከተለያዩ እስፖርት ዉድድሮች ባሻገር፣ የአለምን ህዝብ የሚያገናኝ ታላቅ የባህል መድረክ እንደሆነ ይነገርለታል። በዕለቱ ዝግታችን የኦሎምፒክ ታሪካዊ ዳራዉን ይዘን፣ ባህላዊ ጎኑን እያየን፣ የኢትዮጵያን የኦሎምፒክ ተሞክሮን እንዳስሳለን።

በኦሎምፒክ በተለያዩ ስፖርት ዘርፎች ከአለም አገራት የተሰባሰቡ በሺዎች የሚቆጠሩ ስፖርተኞች የሚያሳትፍበት የዉድድርና እና የባህል መድረክ ነዉ።ኦሎምፒክ ሲነሳ በዘንባባ የተሰራ ተክሊልና የዘንባባ ዝንጣፊ ብሎም ግሪክን የሚያስብ ጥቂት አይደለም። ዘንድሮ ለንደን ላይ በሚደረገዉ 30ኛዉ የኦሊምፒክ ስፖርት ዉድድር ላይ ኢትዮጵያ 64 ስፖርተኞችን እንደምታሰልፍ ተንግሮአል። የኦሎምፒክ ጨዋታ ዉድድር መቼ ተጀመረ? በኢትዮጵያ ስፖርት ፊዴረሽን ለረጅም ግዜ ያገለገሉና፥ በአለማቀፍ የኦሊምፒክ ኮሚቴ ዉስጥ አንዱ ዋና ስራ አስኪያጅ የነበሩት አቶ ፍቅሩ ኪዳኔ ኦሎምፒክ ይላሉ,

The Olympic rings are seen atop the iconic Tower Bridge in London, after they were lowered into position, coinciding with one month to go until the start of London 2012 Games, Wednesday, June 27, 2012. The giant rings, which are fully retractable to allow for tall ships to pass through the bridge, will remain in position for the duration of the Games. (Foto:Lefteris Pitarakis/AP/dapd)
ለንደር ታዋቂዉ ታወር ድልድይ የኦሎምፒክ አርማ 2012ምስል AP

«የኦሎምፒክ እንቅስቃሴ እ,አ,አ 1894 ፓሪስ ዉስጥ በሚገኘዉ በሶርቦን ዩንቨርስቲ ፔር ደ ኩቨርተ በሚባል አንድ ፈረንሳዊ መምህር የተቋቋመ ነዉ። በእዚሁ አ,ም በተደረገዉ ስብሰባ ላይ አቴንስ ግሪክ ላይ የመጀመርያዉ ኦሎምፒክ ጨዋታ እንዲካሄድ ተወስኖ፣ የመጀመርያዉ ዉድድር አቴንስ ከተማ ላይ ተካሄደ። በመጀመርያዉ የኦሎምፒክ ዉድድር ላይ ስፖርተኞች ብቻ ሳይሆኑ ሰአሊዎች መሃንዲሶች የተለያዩ ስራዎቻቸዉን አቅርበዉ ዉድድር አድርገዋል በዚህም ኦሎምፒክ የስፖርት ብቻ ሳይሆን የባህል መድረክም ነዉ።»

በፈረንሳይ አገር ነዋሪ የሆኑት አቶ ፍቅሩ ኪዳኔ በአሁኑ ግዜ በተለያዩ ስፖርት ጉዳዮች በአማካሪነት ይሰራሉ፣ እ,አ 1896 ለመጀመርያ ጊዜ በግሪክ በተካሄደዉ ዉድድር ላይ 11 አገራት ተካፋይ ነበሩ። ኢትዮጵያስ? የኢትዮጵያን ስፖርት ያቋቋሙት የአቶ ይድነቃቸዉ ተሰማ ልጅ አቶ ታደለ ይድነቃቸዉ ኢትዮጵያ ይላሉ

« ኢትዮጵያ በኦሎምፒክ አለም ለመሳተፍ ከገቡ አገሮች መካከል በጣም በጣም ዘግይተዉ ከገቡ አገሮች መካክል ትመደባለች። ከግብፅ ጋር እንኳ ካስተያየነዉ ኢትዮጵያ ለመጀመርያ ግዜ እ, ኢ,አ በ1948 ዓ,ም በሜልቦርን ኦስትሪልያ የኦሎምፒክን መንድረክ ስትቀላቀል ግብፅ ግን እ,አ በ1916 ዓ,ም ነዉ የተቀላቀለችዉ። ያ ማለት ግብፅ በ32 አመት ትቀድመናለች። ሌሎቹ የአፍሪቃ አገሮች ከቅኝ ግዛት ነፃ ስላልወጡ አትሌቶቻቸዉ ኦሎምፒክን የሚወዳደሩት በቅኝ ገዥዎቹ አገር ባንዴራ ስር ሆነዉ ነበር»

An English style phone booth stands outside the building housing the English delegation in the Athletes village in Beijing , China, Sunday, July, 27, 2008.The Olympic village, which opened today will house about 16,000 athletes. .AP Photo/ Elizabeth Dalziel)
እ,ጎ,አ 2008 የቻይናዉ የኦሎምፒክ መንደርምስል AP

ዉድድሩ ሳይጀመር በርካታ አገራት ከኦሊምፒኩ ዉድድር ወደ አገራቸዉ ይዘዉ የሚመለሱትን ሜዳሊያ ቁጥር መተንበይ ጀምረዋል። ጀርመንም በኩልዋ በርከት ያለ ሜዳልያን ለመሰብሰብ ያላትን ምኞት ስንቋን አልደበቀችም። በቀድሞዎቹ አመታት ከሜዳልያ ሽልማቱ ጋር የዘንባባ ተክሊል ማጥለቅ ባህል በኦሊምፒክ ይታይ ነበር። 1948 ዓም ኢትዮጵያ በሜልበርኑ የኦሎምፒክ አደባባይ አሃዱ ብላ ገብታ በመቀጠል በሮሙ ኦለምፒክ የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የአፍሪቃ የጥቁር ህዝብ የኮራበትን ታሪክ ፃፈች። ሙሉዉን ቅንብር ያድምጡ!

አዜብ ታደሰ

አርያም ተክሌ