1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኦሎምፒክ የህዝብ ጨዋታ

ቅዳሜ፣ ሐምሌ 21 2004

የለንደኑ የ2012 የኦሎምፒክ ውድድር የልሂቃን ብቻ ሳይሆን ማንኛውም ሰው የሚደሰትብት ጨዋታ መሆኑን የብሪታኒያ ባለሥልጣናት አበክረው ያስገነዝባሉ ። በመክፈቻው ስነ ስርዓት ላይ እንኳን የብሪታኒያን ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ስብጥር ለማንፀባረቅ ተማሪዎች ነርሶችና ሌሎች ተራ ዜጎች ሁሉ እንዲሳተፉ ይደረጋል ።

https://p.dw.com/p/15f5B
The Olympic rings are seen atop the iconic Tower Bridge in London, after they were lowered into position, coinciding with one month to go until the start of London 2012 Games, Wednesday, June 27, 2012. The giant rings, which are fully retractable to allow for tall ships to pass through the bridge, will remain in position for the duration of the Games. (Foto:Lefteris Pitarakis/AP/dapd)
ምስል dapd

ነገ የሚጀመረው የለንደኑ የ2012 የኦሎምፒክ ውድድር የልሂቃን ብቻ ሳይሆን ማንኛውም ሰው የሚደሰትብት ጨዋታ መሆኑን የብሪታኒያ ባለሥልጣናት አበክረው ያስገነዝባሉ ። በመክፈቻው ስነ ስርዓት ላይ እንኳን የብሪታኒያን ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ስብጥር ለማንፀባረቅ ተማሪዎች ነርሶችና ሌሎች ተራ ዜጎች ሁሉ እንዲሳተፉ ይደረጋል ። ይሁንና በሌላ በኩል ጨዋታዎቹን በስፍራው ተገኝቶ ለመከታተል የሚያስችል ቲኬት ማግኘት ግን እንዲህ ቀላል ሆኖ አልተገኘም ። ከዚህ ሌላ የለንደን ነዋሪዎች በጨዋታው ወቅት በከተማዋ እንደ ልብ መዘዋወር አዳጋች ሊሆንባቸውም ይችላል ። የዶቼቬለ የለንደን ወኪል ኒና ማርያ ፖትስ ያቀረበችውን ዘገባ ሂሩት መለሰ አጠናቅራዋለች ።

የለንደኑን ኦሎምፒክ በስፍራው ተገኝተው ለማየት ቲኬት የማግኘት ችግር ገጥሞዎት ከሆነ ይህ የርስዎ ችግር ብቻ አይደለም ትላለች ኒና ማርያ ። ከአጠቃላዩ 8.8 ሚሊዮን የኦሎምፒክ ጨዋታዎች የመግቢያ ቲኬቶች 7 ሚሊዮኑ ካለፈው አመት አንስቶ እስካለፈው ሰኔ ድረስ በኢንተርኔት በተካሄደ ጨረታ ተሸጠው አልቀዋል ። የዋና ዋናዎቹ ማራኪ ውድድሮች የመግቢያ ቲኬቶችም ከአሁኑ በውድ ዋጋ በጥቁር ገበያ ቀርበዋል ። በሌላ በኩል ደግሞ ከብዙዎች አቅም ባላይ የሆነ ዋጋ ያላቸው በርካታ ቲኬቶችም ይገኛሉ ። ከቲኬቶች ሽያጭ ጋር ተያይዘው የሚቀርቡ የተለያዩ ወቀሳዎችን የኦሎምፒክ አትሌቲክስ ኮሚቴ ሊቀመንበር ጆናታን ኤድዋርድስ ያስተባብላሉ ።

Olympia London 2012 Symbolbild
ምስል picture-alliance/dpa

« ከቲኬቶች ጋር የተያያዘው ጉዳይ ቀላል ነው ። ለሽያጭ ከቀረበው ቲኬት በላይ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ናቸው ቲኬት የሚፈልጉት ። ይህ ለኛ ለአዘጋጁ ኮሚቴ እፁብ ድንቅ ዜና ነው ። ምክንያቱም 25 በመቶ ገቢያችንን የምናገኘው ከቲኬት ሽያጭ ነው ። ለአለም ዓቀፉ አዘጋጅ ኮሚቴና ለአለም አትሌቶች ቃል ከገባናቸው ጉዳዮች ውስጥ አንዱ በህዝብ በተሞላ ስታድዮም ውድድሮቹን እንደሚያካሂዱ ነው ። የሚያገኙትም ይህንኑ ነው ። ይህ ደግሞ በእውነት ለአትሌቶቹም አስፈላጊ ነው ። »

ከዚህ ሌላ ኤድዋርድስ እንደሚሉት ከውድድሮቹ በተጨማሪ የሚካሄዱ ሌሎች የባህል መርሃ ግብሮችም ትኩረት ሊሰጣቸው የሚችል ህዝብን ይበልጥ የሚያሳትፉ ዝግጅቶች ናቸው ። ይሁንና ሁሉም ነዋሪዎች ተመሳሳይ ስሜት የላቸውም ። ለምሳሌ በኦሎምፒክ ፓርክ አቅርቢያ በሚገኘው በኒውሃማ የሚገኙ ነዋሪዎች ከተጠቀሱት ዝግጅቶች አንዱም የሚያመጣላቸው ጥቅም ያለ አይመስላቸውም ። የኦሎምፒክ ባለሥልጣናት ግን በተራ ዜጎች በተዘጋጁ ልዩ ልዩ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ሁሉም መካፈል ይችላል ባይ ናቸው ። ጆን አርሚት ከባለሥልጣናቱ አንዱ ናቸው ።

Volunteers with Umbrellas stand in front of the Olympic Stadium in London, Britain, 18 July 2012. The London 2012 Olympic Games will start on 27 July 2012. Photo: Michael Kappeler dpa pixel
ምስል picture-alliance/dpa

« በለንደን የተለያዩ አካባቢዎች በግሪንዊች መናፈሻ በማዕከላዊ ለንደን በ whitewall በ Horse Guards parade ና በ Hyde መናፈሻ እጅግ ብዙ ዝግጅቶች ይካሄዳሉ ። በ Stratford ብቻ ሳይሆን ለንደን ውስጥ በሌሎችም ስፍራዎች እንቅስቃሲዎች የሚካሄዱባቸው ቦታዎች አሉ ። ይህ ህዝብን እጅግ የሚያቀራርብ መናፈሻ ነው ። ሰዉ የግድ ቲኬት መግዛት አይኖርበትም ። ስታድዮምም መገኘት የለበትም ። ወንዙን እና የመልከዓ ምድሩን አቀማመጥ እያደነቀ በትላልቅ ቴሌቪዥኖች ጨዋታዎቹን እየተከታተለ በተመሳሳይ ጊዜ የሚካሄዱትንም ባህላዊ እንቅስቃሴዎች ማየት ይችላል ። ሰዉ ሊዝናናባቸው የሚችል በርካታ እንቅስቃሲዎች ይኖራሉ »

ያም ሆኖ ውድድሩ በሥራቸው ላይ ተፅዕኖ የሚያደርግ የህብረተሰብ ክፍሎች ቅር መሰኘታቸው አልቀረም ። አንዳንድ የለንደን መንገዶች በከፊል ለትላልቅ እንግዶችና ለኦሎምፒክ ባለሥልጣናት ተለይተው መያዛቸው የለንደን የታክሲ ሾፌሮችን አበሳጭቷል ። እርምጃው ገበያችን ያዳክማል ነው የሚሉት ። የለንደን ታክሲ ሾፌሮች ማህበር ቃል አቀባይ ስቲቭ ማክናማራ

The Olympic rings are seen atop the iconic Tower Bridge in London, after they were lowered into position, coinciding with one month to go until the start of London 2012 Games, Wednesday, June 27, 2012. The giant rings, which are fully retractable to allow for tall ships to pass through the bridge, will remain in position for the duration of the Games. (Foto:Lefteris Pitarakis/AP/dapd)
ምስል AP

«ኦሎምፒክ በጣም ተፅዕኖ ያሳድርብናል ። የሚዘጋው የመንገድ ክፍል ስፋት እኛን በጣም ከሚያሳስቡን ጉዳዮች አንዱ ነው ። አብዛኛዎቹ የለንደን ዋና ዋናዎቹ መንገዶች በከፊል ይታገዳሉ ። እንደሚመስለኝ 38 ማይል ይሆናሉ ። እነዚህን መንገዶች መጠቀም አንችልም ። በዚህ ተበሳጭተናል ። »

ጨዋታው ከተጀመረ በኋላ የለንደን ነዋሪዎች ቲኬት ኖራቸውም አልኖራቸው የውድድሮቹን ውጤቶች በትጋት ይከታተላሉ የኦሎምፒክ መንፈስም ያድርባቸዋል የሚል ተስፋ አለ ። ዘንድሮ የኦሎምፒክ ውድድር ቲኬት ከሌላቸውና በዚህም ውድድር እለታዊ ኑሮአቸው ከሚታወከው ሌላ ውድድሩ የሚስበው ምን ያህሉ እንደሆነ በተጨማሪ የሚነሳ ጥያቄ ነው ።

ሂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ