ኦሊምፒክና ሥነ ቴክኒክ
ረቡዕ፣ ሐምሌ 18 2004አስመዝግቦ፤፣ ምን ዓይነት አስተዋጽዖስ አድርጎ ይሆን?! ሥነ ቅመማው (ኬምስትሪው) በአትሌቶች አመጋገብ፤ ፊዚክሱ፤ በማንኛውም የውድድር ዓይነት ፤ ፍጥነትን ፤ ከፍታን የአየር ግፊትን ፣ የስበት ኃይልን ሲዳስስ፤ ሥነ ህይወቱ፤ የስነ ልቡና ይዞታን፤ የደም ዝውውርን ፣ እስትንፋስን፣ ሙቀትን ብርድን፣ በአጠቃላይ የጤንነት ይዞታን ሊመለከት ይችላል።
«ዲስከስ» ውርወራ፤ መዋኛ ኩሬን በፍጥነት ሰንጥቆ የመሻገሩ ዘዴ ፣ ሽምጥ ሩጫው፣ የአጭርና ረጅም ርቀት አሯሯጥ፣ የምድርና የአየር ዝላይ፣ ለቅርጫትና መረብ ኳስ፤ ለቴኒስ፤ ለእነዚህና ለመሳሰሉት ሁሉ የእስፖርት ዓይነቶችም ፣ በተለያየ የአየር ጠባይ ተስማሚ የሆኑ የእስፖርት መሣሪያዎችንና መጫሚያዎችን የማሰናዳቱን ፣ ውጤትም የማስመዝገቡን ብልሃት፤ ይህ ሁሉ ፣ ሳይንስን ፤ ሥነ ቴክኒክን፣ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ማጣቀሱ ያለ ጉዳይ ነው። እስፖርት፤ በተለይ ም የውድድር እስፖርት፤ ሂሳብንም ፤ ሳይንስንም መሠረት ያደርጋል።
ዝነኛው ዓለም አቀፍ አትሌት ፤ ኃይሌ ገ/ሥላሴ፣ አንድ ጊዜ ለራዲዮ ጣቢያችን፣ ሩጫ እንዲሁ ሩጫ አይደለም ፤ ስሌት ያለበት ሂሳብ ነው፤ ያለውን ያስታውሷል። ሥነ ቴክኒክ ለእስፖርት ስለሚያበረክተው ድርሻ፣ በለንደን ኑዋሪ የሆነው የቅርጫት ኳስ ተጫዋችና አሠልጣኝ ሳሙኤል ብርሃኑ--
ከተለያዩ ፣ ለእስፖርት ከሚጠቅሙ መሳሪያዎች ባሻገር በቀጥታ አትሌቶች የሚገለገሉባቸው ጫማዎች ፣ ለሩጫም ሆነ ለአግር ኳስ፣ ቅርቻት ኳስ፣ መረብ ኳስ፣ ቴኒስና ለመሳሰለው በየጊዜው እየተሻሻሉ መሠራታቸው አልቀረም። የአካል ጉዳተኞች ለሆኑ እስፖርተኞች ይጠቅማሉ የሚባሉ ልዩ - ልዩ የጫማ ዓይነቶችም ይቀርባሉ። በጀርመን ሀገር ፣ኑዑረንበርግ ከተማ አቅራቢያ የሚገኘው የአዲዳስ ኩባንያ፣ በበኩሉ ለሽምጥ ሯጮች የሚበጅ 99 ግራም ብቻ የሚመዝን ጫማ ሠርቼአለሁ ማለቱን ሰምተናል፤ በጋዜጣም አንብበናል። ከእግር ጣቶች እስከ ተረከዝና ቁርጭምጭሚት ፣ ጉዳት የማያስከትል የማያቆስል፤ ፍጥነትንም የማይገታ ፤ ፍጹም ወደር የሌለው ጫማ፤ እውን ቀርቦ ይሆን?! ስለ እስፖርት ጫማ፣ ፈጣን እንቅሥቃሤ የሚደረግበት የቅርጫት ኳስ ተጫዋችና አሠልጣኝ ሳሙኤል እንዲህ ይላል።
ተክሌ የኋላ
አርያም ተክሌ