እስራኤልና ፍልስጤም የሰላም ዉይይት
ማክሰኞ፣ ነሐሴ 7 2005ማስታወቂያ
በጎርጎሪዮሳዊዉ 2010 ዓ,ም ተቋርጦ የነበረዉ የእስራኤል እና የፍልስጤም የሰላም ድርድር፤ አሜሪካን ለወራት ካደረገችዉ ጥረት በኋላ፤ የሁለቱም ወገን ተደራዳሪዎች ከሳምንት በፊት ዋሽንግተን ላይ፤ ለዉይይት መገናኘታቸዉ ይታወቃል። የሰላም ዉይይቱ የድንበር ማካለልን ጨምሮ የኢየሩሳሌም እና የተመዘገቡ 5,3 ሚሊዮን ፍልስጢማዉያን ስደተኞች የወደፊት እጣ ፈንታ ፤ እንዲሁም የእስራኤል የፀጥታ ሁኔታ ላይ እንደሚያተኩር ይጠበቃል። እስራኤል ከእስር የምትለቃቸዉን የ 26 ፍልስጤማዉያን እስረኞች ስም ዝርዝር ይፋ አድርጓል ። በእየሩሳሌም የሚገኘዉን ወኪላችን ዜናነህ መኮንንን ስለሰላም ዉይይቱ በስልክ ጠይቄዉ ነበር።
ዜናነህ መኮንን
አዜብ ታደሰ
ሒሩት መለሰ