እስራኤልና አፍሪቃዉያን ስደተኞች
ሰኞ፣ ሐምሌ 19 2002ማስታወቂያ
የከተማዋ ኗሪዎች ኤርትራዉያንም ሆኑ ሱዳናዉያን ስደተኞች ለሥራ ፍለጋ አገራችን የገቡ ናቸዉ የሚል ስሜት ያንፀባርቃሉ። ስደተኞቹ ቁርማርተኛ፤ ሰካራም፤ ዘራፊ፤ እንዲሁም አደገኛ እፅ አዘዋዋሪ ናቸዉ ብለዉም ይተቻሉ። በእስራኤል የጥምሩ መንግስት አባል የሻዝ ፓርቲ በኅብረተሰቡ ዉስጥ ተሰራጭተዉ የሚገኙ አፍሪቃዉያን ስደተኞችን በሚመለከት ለቀረበዉ ጥያቄ ትክክለኛ መፍትሄ ካልሰጡ ጥምር መንግስቱን ለቆ እንደሚወጣ ለጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ናታንያሁ ማሳሰቢያዉን አቅርቧል።
ዜናነህ መኮንን፤
ሸዋዬ ለገሠ
ሂሩት መለሰ