እስላማዊ ትብብር ድርጅት እና ሶርያ
ማክሰኞ፣ ነሐሴ 8 2004ማስታወቂያ
ይህ በሳዑዲ አረቢያ ንጉስ አብደላ ቢን አብደል አዚዝ አሳሳቢነት በአስቸኳይ የተጠራው እና 57 አባል ሀገራትን ያቀፈው የዓለም አቀፍ የሙስሊም ሀገራት ትብብር ጉባኤ ትናንት ማምሻውን ነበር በመካ የጀመረው። ጉባኤው ዛሬም ቀጥሎ ውሏል። በዚሁ ስብሰባ ላይ ለመገኘት የኢራኑ ፕሬዚዳንት አህመዲን ነጃድን ጨምሮ በርካታ የሙስሊም እና የአረብ ሐገራት መራሄ-መንግስታት ትናትና እና ከትናት በስተያ መካ መግባታቸውም ተዘግቧል። የሳዑዲ አረቢያ ወኪላችን ነቢዩ ሲራክ ጉባኤውን ቃኝቶ የሚከተለውን ዘገባ ልኮልናል።
ነቢዩ ሲራክ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ሸዋዬ ለገሰ