ኤች.አይ.ቪ የታወቀበት ሠላኛ ዓመት
ዓርብ፣ ሰኔ 3 2003ማስታወቂያ
ኤድስ የሚያመጣዉ ቫይረስ ኤች.አይ.ቪ የታወቀበት ሠላሳኛ አመት በተለያዩ ሐገራት በተለያዩ ሥነ-ሥርዓቶች እየታሰበ ነዉ።ቫይረሱ ዩናይትድ ስቴትስ ዉስጥ በመታወቁ የሐገሪቱ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ወይዘሮ ሒላሪ ክልተን ሰላሳኛዉን አመት ምክንያት በማድረግ ባሥተላለፉት መልዕክት የበሽታዉን ሰለቦችና ቤተ-ሠቦቻቸዉን ለመርዳት የሚመደበዉ ገንዘብ መጨመር እንዳለበት አሳስበዋል።አዲስ አበባ ዉስጥም የኤች አይ ቪ ኤድስን ሥርጭትና ሥርጭቱን ለመግታት ሥለሚደረገዉ ጥረት የተነጋገረ ስብሰባ ትናንት ተደርጎ ነበር።ወኪላችን ጌታቸዉ ተድላ ስብሰባዉን ተከታትሎ ዘገባ ልኮልናል።
ጌታቸዉ ተድላ
ነጋሽ መሐመድ
ተክሌ የኋላ