1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኤርትራዊዉ አሜሪካዊ የተፈፀመበት ግፍ

ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 16 2004

በትዉልድ ኤርትራዊ በዜግነት አሜሪካዊ የሆነዉ ቶማስ ፍቅሬ አቡዳቢ ዉስጥ ታስሮ መገረፍ፥ መሰቃየት፥ እና ከተለቀቀ በሕዋላ ወደ አሜሪካ እንዳይገባ መከልከሉን አስታወቀ። በትዉልድ ኤርትራዊ በዜግነት አሜሪካዊ የሆነዉ ቶማስ ፍቅሬ

https://p.dw.com/p/14kLd
Federal Bureau of Investigation Logo

አቡዳቢ ዉስጥ ታስሮ መገረፍ፥ መሰቃየት፥ እና ከተለቀቀ በሕዋላ ወደ አሜሪካ እንዳይገባ መከልከሉን አስታወቀ።ቶማስና ጠበቃዉ እንደሚሉት ቶማስ ከአንድ መቶ ቀናት በላይ ታስሮ ሲለቀቅ የተመሠረተበት ክስ አልነበረም።እስር ቤት በነበረበት ወቅት ደግሞ የአሜሪካ ማዕከላዊ ቢሮ (FBI) ባልደረቦች ወይም ተባባሪዎች ናቸዉ ብለዉ የሚጠረጥሯቸዉ ሰዎች ይገርፉት፥ ያሰቃዩት እና ለFBI እንዲሰልል ያስፈራሩት ነበር።የአሜሪካ እስላማዊ ምክር ቤት ቃል አቀባይ ኢብራሒም ሑፐር እንደሚሉት በቶማስ ላይ የተፈፀመዉ አይነት ግፍ በብዙ አሜሪካዉያን ሙስሊሞች ላይ በተደጋጋሚ እየተፈፀመ ነዉ።

አበበ ፈለቀ

ነጋሽ መሀመድ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ