ኢ ሠ መ ጉ ና መግለጫው
ሐሙስ፣ የካቲት 1 2004ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባዔ፣(ኢ ሠ መ ጉ)የአፍሪቃ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ በተካሄደበት ሰሞን፤ ከተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብት ጽ/ቤትና ፤ ከአፍሪቃ ኅብረት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ጋር፤ በሰብአዊ መብትና በአህጉሩ መሰል ድርጅቶች ተግባር ላይ መወያያቱ ተነግሯል። ኢ ሠመ ጉ ፣ የልማት እንቅሥቃሤዎች፤ የዜጎችን መሠረታዊ መብቶች የሚያሳጡ መሆን የለባቸውም በሚል ርእስ 20 ገጾች ባሉት ጥራዝ ያጠናቀረውን ሰብአዊ መብት ነክ ዘገባ አቅርቧል። ጌታቸው ተድላ ኃ/ጊዮርጊስ ፤ ከዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች ጋር ስለተደረገው ምክክር የኢሠመጉን ሊቀመንበር አቶ እንዳልካቸው ሞላን በማነጋገር የሚከተለውን ዘገባ ልኮልናል። አቶ እንዳልካቸው እንዲህ በማለት ነው ማብራሪያቸውን የሚጀምሩት ።
ጌታቸው ተድላ ሃ/ጊዮርጊስ
ተክሌ የኋላ
ነጋሽ መሐመድ