1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢድ-አልአዳህ፣ መካን ለሃጂ ጸሎት

ዓርብ፣ ታኅሣሥ 11 2000

በያዝነዉ ሳምንት 3 ሚሊዮን ሙስሊሞች ቅዱስ ከተማይቱን መካን ለሃጂ ጸሎት ጎብኝተዋል። አራት ቀን ያህል የፈጀዉ መንፈሳዊ ጉዞ እንዳይታወክ ከፍተኛ ጥበቃ ተደርጎ ነበር። ኢትዮጽያዉያን ሙስሊሞችም የዘንድሮዉን ኢድ አል አላዳህን በደማቅ ሁኔታ አክብረዋል

https://p.dw.com/p/E0lv
ምስል picture-alliance/ dpa
ከአለም ዙርያ የተሰባበቡ ሙስሊሞች ነጭ እና ረጅም ጀልቢያ ለብሰዉ መካን ጸሎት በማድረስ ጎብኝተዋል። በዘንድሮዉ መንፈሳዊ ጉዞ ላይ የኢራኑ መሪ አህመዲን ነጃድ መገኘታቸዉ የምዕራባዉያኑን የዜና አዉታር ቀልብ ስቦ ነበር። አህመዲን ነጃድ በሳዉዲ አረብያዉ ንጊስ አብደላ ግብዣ የአረፋ ቀን ከመዋሉ አንድ ቀን ቀደም ብሎ ማለት ባለፈዉ ሰኞ ነበር በመዲና የተገኙት አረፋ የሚለዉ ቃል ምን ማለት ይሆን ኢድ አላዳህ በአልስ በአዲስ አበባ የፈቱህ መስጊድ ኢማም፣ በአወልያ ኮሌጅ የአረብኛ ቋንቋ መምህር የሆኑት ሼህ ሙሃመድ ሃሚዲን ይገልጹልናል። በተጨማሪ በጉራጌ ብሄረሰብ ዘንድ የኢድ አላዳህ በአል አከባበር ለየት ማለቱን የሚነግሩን የቤት እመቤቶችም ጋብዞአል መልካም ቆይታ