ኢንዶኔዥያዊቷ የቤት ሰራተኛ የደረሰባት በደል
ማክሰኞ፣ ሰኔ 21 2003ማስታወቂያ
በአሁኑ ሰዓት ከቀያቸው ርቀው በየሃገሩ በቤት ሰራተኝነት ለጉልበት ብዝበዛ የተዳረጉ ፣ ለጤና እክል የተጋለጡ ችግሩም ሲከፋም ህይወታቸውን እሰከማጣት የደረሱ እና ሳይወዱ በግዳጅ በዝሙት የተሰማሩም ሴቶች ቁጥር ከፍተኛ ነው ። ሴቶች ለዚህን መሰሉ ችግር በስፋት ከተጋለጡባቸው አካባቢዎች ውስጥ መካከለኛው ምሥራቅ በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳል ። ወደ አረብ ሃገራት በህጋዊም ይሁን በህገ ወጥ መንገድ የሄዱ እህቶች ኢትዮጵያውያን ጨምሮ ለነዚህ ችግሮች እንደሚዳረጉ በተደጋጋሚ የተነገረ ጉዳይ ነው ። ችግሩ ግን በነዚህ ሃገራት ብቻ የተወሰነ አለመሆኑን አልፎ አልፎ በአውሮፓ እና በአሜሪካንም ደረሱ ከሚባሉ ተመሳሳይ ክስተቶች መረዳት ይቻላል ። ለዚህም ጀርመን መዲና በርሊን በአንድ ዲፕሎማት ቤት ውስጥ በሰራተኝነት ስታገለግል በነበረች ኢንዶኔዥያዊት ላይ የተፈፀመው በደል አንድ ምሳሌ ሆኖ ቀርቧል።
ሂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ