ኢንዶኔዢያ፦በ1 ቤተሰብ አባላት ጥቃት በርካቶች ሞቱ
እሑድ፣ ግንቦት 5 2010ማስታወቂያ
ሁለት ልጆችን ጨምሮ ስድስት አባላት ያሉት አንድ ቤተሰብ ኢንዶኔዥያ ውስጥ በሚገኙ በሦስት አብያተ ክርስቲያን አስከፊ የተባለ የአጥፍቶ መጥፋት ጥቃት መፈጸሙን ፖሊስ አስታወቀ። ሱራባያ በተባለችው ከተማ በተፈጸመው ጥቃት ሰባት ሰዎች እና ስድስቱ አጥፍቶ ጠፊዎች ተገድለዋል። 41 ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል። የአገሪቱ ፖሊስ አዛዥ ቲቶ ካርናቪያን እንዳሉት አባትየው በመኪና በተጠመደ ቦምብ፣ እድሜያቸው 18 እና 16 የሆነ ሁለት ልጆች በሞተር ሳይክል ጥቃቱን ፈፅመዋል። እናት ዕድሜያቸው 12 እና 9 ከሆነ ልጆቻቸው ጋር ሆነው ሌላ ጥቃት ፈፅመዋል። ካርናቫያን እንዳሉት ጥቃት ፈፃሚዎቹ ከሶርያ ወደ ኢንዶኔዥያ የተመለሱት በቅርቡ ነበር። ራሱን «እስላማዊ መንግሥት» ብሎ የሚጠራው ጽንፈኛ ታጣቂ አማቅ በተባለ ልሳኑ በኩል ኃላፊነት ወስዷል። ታጣቂ ቡድኑ ጥቃቱን ስለፈጸመው ቤተሰብም ሆነ ስለ ልጆቹ ያለው ነገር የለም።
እሸቴ በቀለ
ማንተጋፍቶት ስለሺ