ኢትዮጵያ-የአነሳ ብሔረሰቦች መብትና ወቀሳዉ
ረቡዕ፣ ጥቅምት 1 2004ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ፌደራላዊ መንግሥትና የክክልል መስተዳድሮች ኢትዮጵያዊነታችንን እያጠራጠሩን፥ ሕገ-መንግሥታዊ መብታችንንም እየጣሱብን ነዉ በማለት የተለያዩ ማሕበረሰብ ተወካዮች አማረሩ።የዳጣ፥ የዱቤና የሌሎች አነሳ ማሕበረሰብ ተወካዮች እንደሚሉት መብታቸዉን ለማስከበር ላለፉት ሃያ አመታት ቢሟገቱም እስካሁን መፍትሔ አላገኙም።ተወካዮቹ እንደሚሉት የአካባቢያዊ መስተዳድሮች ባለሥልጣናት የማሕበረሰቡ አባላትን ይበድላሉ፥ከሥራ ያፈናቅላሉ፥ የማሕበረሰቡ አባላት በብዛት በሚኖርበት አካባቢም የመሠረተ ልማት አዉታር እንዳይዘረጋ ያከላክላሉም።የኢትዮጵያ የፌደሬሽን ምክር ቤት ጉዳዩ እየተጠና ነዉ ባይ ነዉ።ታደሰ እንግዳዉ ዝር ዝር ዘገባ አለዉ።
ታደሰ እንግዳዉ
ነጋሽ መሐመድ
ሸዋዬ ለገሰ