1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት መግለጫ

ሐሙስ፣ ጥቅምት 27 2012

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በመጭው ቅዳሜ የሚከበረውን 1494 ኛውን የመውሊድ በዓል አስመልክቶ ለመላው ሙስሊም ኢትዮጵያዊ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፈ። የጠቅላይ ም/ቤቱ ፕሬዝዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጂ ዑመር በኢትዮጵያ በዚህ ዓመት የሙስሊም አንድነት ብለን የጀመርነው ሥራ «በዓለም የሌለ አንድነት ነው» ብለዋል።

https://p.dw.com/p/3SdvG
Äthiopien Haji Umer Indris
ምስል DW/S. Muchie

«የጠቅላይ ምክር ቤቱ መግለጫ»

 

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በመጭው ቅዳሜ የሚከበረውን 1494 ኛውን የመውሊድ በዓል አስመልክቶ ለመላው ሙስሊም ኢትዮጵያዊ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፈ። ምክር ቤቱ ነብዩ ሙሃመድ አንድነትን ያስተማሩ፣ ህዝባቸውን በወንድማማችነት ያስተሳሰሩ፣ ጥላቻን አውግዘው ፍቅርንና ሰላምን አብዝተው የሰበኩ ናቸው። መውሊዱም በሃገራችን ጨምሮ በዓለማት በብሔራዊ ደረጃ የመከበረል ምክንያት ይሄው ነው ብሏል። ምክር ቤቱ ከፌደራሉ ጀምሮ የክልል እና የከተማ መስተዳድር መጅሊሶችን እያዋቀረ ቢሆንም ማዕከልን ባልጠበቀ አኳኋን የመጅሊስ ምክር ቤቶችንና እና መስጅዶችን የመንጠቅ በከተሞች ኢማሞችንና ሙአዚኖችን ፤ በገጠር መሻኢኮችንና ሙደሪሶችን ያማስከፋት፣ ከሥራ የማፈናቀል ድርጊት ገጥሞኛል ብሏል። የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጂ ዑመር ኢድሪስ ለእምነቱ ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ካስተላለፉ በኋላ በኢትዮጵያ በዚህ ዓመት የሙስሊም አንድነት ብለን የጀመርነው ሥራ «በዓለም የሌለ አንድነት ነው» ብለዋል። የሃይማኖት ልዩነት ያላቸው ሰዎች በዓለም አንዱ የበላይ አንዱ የበታች ሆኖ ይኖራል እንጅ ሁለቱ በአንድ ቢሮ አንድነህ ፈጥረው በሰላም መሄድ በእኛ ሃገር ብቻ የተጀመረ ነው ሲሉ ተናግረዋል። ይህንን ነገር ስንጀምረው «ሰለፍያ» እና «ሱፊያ» የሚባሉ ነገሮች ነበሩ ያሉት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጂ ዑመር ሁለቱም እኩል ሆኖ እንዲመራ ነው ያደረግነው። አሁን ግን በኦሮሚያ ስንሄድ በአጠቃላይ ሰለፍያ ብቻ ነው የተመረጠው ይህም ችግር መስተካከል አለበት ብለዋል። ችግሩ በደቡብም የተስተዋለ ቢሆንም ማስተካከላቸውንም አመልክተዋል። በሌላ በኩል በሃረሪ ፣ ሶማሌ እና ድሬዳዋ እኛ ከመመረጣችን በፊት የፊቱን መጅሊስ ገልብጦ ሕገ ወጥ መጅሊስ ነው ያለው ያንንም ለማስተካከል ተዘጋጅተናል ብለዋል። ከአዲስ አበባ ዘጋባያችን ሰለሞን ሙጬ ዝርዝሩን ልኮልናል።

ሰለሞን ሙጬ
አዜብ ታደሰ 
ነጋሽ መሐመድ