ኢትዮጵያውያን በካን የፊልም ፌስቲቫል
ዓርብ፣ ግንቦት 22 2006ማስታወቂያ
ያምሮት ንጉሤ፣ ሔርሞን ኃይላይ፣ ሕይወት አድማሱ፣ አዳነች አድማሱ እና ዳንኤል ደበበ ናቸው ታዳሚያኑ። የካን የፊልም ፌስቲቫል፤ ከግማሽ ምዕተ-ዓመት በፊት ሲቋቋም፣ ለሲኒማ ጥበብ እድገት አስተዋፅዖ ያደረጉ ባለሙያዎችን እና ሥራዎቻቸውን በማስተዋወቅ ሲኒማን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማክበር በሚል መርኅ ነው። እጎአ በ1946 ዓም የተቋቋመው ይኽ የካን የፊልም ፌስቲቫል በየዓመቱ ሲከበር ዘንድሮ 67ኛ ዙር ላይ ደርሷል። በእዚህ የፊልም ፌስቲቫል የተሳተፉት አምስቱም ኢትዮጵያውያን ነዋሪነታቸው በአዲስ አበባ ነው።
ከግንቦት 6 ቀን፣ 2006 ዓም ለ12 ተከታታይ ቀናት በተከናወነው የፊልም ፌስቲቫል ኢትዮጵያውያኑ ለአንድ ሣምንት ያህል በመታደም የተለያዩ ሥልጠናዎችን አግኝተዋል። በፌስቲቫሉ ለመሳተፍ ከ40 በላይ ኢትዮጵያውያን አመልክተው እንደነበር የውድድሩ አዘጋጆች እንደገለፁላቸው ኢትዮጵያውያኑ ታዳሚያን አጫውተውናል።
ወደፊት ሌሎች ኢትዮጵያውያን የፊልም ባለሙያዎች እና ሠራተኞችም በእንደዚህ አይነት ዓለም አቀፍ የፊልም ፌስቲቫሎች ለመሳተፍ ጥረት እንደሚያደርጉ ተስፋ እናደርጋለን። ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ ከታች የሚገኘውን የድምጽ ማጫወቻ ይጫኑ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ተክሌ የኋላ