ስደተኞች በሊቢያ ለወራት ታስረው ነበር ተብሏል
ዓርብ፣ ጥር 18 2010ማስታወቂያ
ሊቢያን በመሸጋገሪያነት ተጠቅመው ወደ አውሮፓ ለመግባት ሞክረው ያልተሳካላቸው ስደተኞች በሰሜን አፍሪካዊቷ ሀገር ለባርነት ከመሸጥ እስከ እስር ያሉ ስቃዮች እየደረሰባቸው ይገኛል፡፡ ከእነዚህ ስደተኞች መካከል በርካታ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን እንደሚገኙበት መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ የዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት (IOM) ከኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ጋር በመተባበር እንግልት የደረሰባቸውን ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ወደ ሀገር ቤት መመለስ ጀምረዋል፡፡
የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ ከሊቢያ ኢትዮጵያውያን እንዲሚለሱ እርዳታ እያደረገ ያለውን የIOM የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አለማየሁ ሰይፈሥላሴን አነጋግሯል፡፡ ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ።
ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ
ሸዋዬ ለገሠ