ኢትዮጵያዊዉ ጋዜጠኛ ተሰደደ
ማክሰኞ፣ ግንቦት 2 2008ማስታወቂያ
«የቀለም ቀንድ» የተሰኘዉ ሳምንታዊ የአማርኛ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ሙሉቀን ተስፋዉ ከሐገር ተሠደደ።ሙሉቀን ከሐገር የወጣዉ ባለፈዉ ሳምንት የተከበረዉን የዓለም የፕረስ ነፃነት ቀንን ምክንያት በማድረግ ፊንላንድ ዉስጥ በተዘጋጀ በዓል ላይ ለመካፈል ነበር።ጋዜጠኛዉ እዚያዉ ኢትዮጵያ እያለ የኢትዮጵያ መንግሥት የፀጥታ ሐይሎች በተደጋጋሚ ያደርሱብኛል ያለዉ ዛቻ፤ ማስፈራሪያ እና ክትትል አዉሮጳ ከገባ በኋላም በባልደረቦቹ፤ በጓደኞቹ እና በቤተሠቦቹ ላይ በመቀጠሉ ለመሰደድ መወሰኑን አስታዉቋል።
ነጋሽ መሐመድ
አዜብ ታደሰ