«ኢትዮጵያዊነት በተግባር» የርዳታ ማኅበር
ሐሙስ፣ ጥቅምት 1 2011ማስታወቂያ
«በሀገራችን የተለያዩ ሥፍር ቁጥር የሌላቸው ችግሮች በመደቀናቸዉ በምንችለዉ ዘርፍ ሀገራችንን እንረዳለን» ሲል የጠቀሰዉ ማኅበሩ፤ በተለይ በአሁኑ ወቅት ለተፈናቃዮች የርዳታ እጁን እንደዘረጋ ነዉ የተገለፀዉ። ኢትዮጵያዊነት በተግባር በካናዳ፤ በአሜሪካ፤ በአዉሮጳ ፤ በመካከለኛዉ ምሥራቅ እንዲሁም በአፍሪቃ ዉስጥ የተለያዩ ሥራዎችን እየሰራ እንደሆነም « DW» ያነጋገራቸዉ በበርሊን ከተማ የማኅበሩ አባልና ተጠሪ ተናግረዋል። በበርሊን ነዋሪ የሆኑት የማኅበሩ ተጠሪ ወ/ት ሰብለ ወንጌል ዓለምሰገድን የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ኃይለ ሚካኤል አነጋግሮ አጠር ያለ ዘገባ ልኮልናል።
ይልማ ኃይለ ሚካኤል
አዜብ ታደሰ
አርያም ተክሌ