ኢትዮጵያን እና ኬንያን የጎበኘዉ የጀርመን የልዑካን ቡድን
ዓርብ፣ የካቲት 2 2004ማስታወቂያ
ወደ ኢትዮጽያ እና ኬንያ በመጓዝ የዶሎ አዶን እንዲሁም ካኩምን የረሃብተኞች ካንፕ ጎብኝቶ የተመለሰዉ የጀርመን ሸንጎ አባሎች የልዑካን ቡድን ስለጉዞዉ በርሊን ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቶአል። ከክርስትያን ዲሞክራቲክ እና ከአረንጓዴዉ ፓርቲ የተዉጣጡት የጀርመን የሸንጎ አባላት አዲስ አበባ ላይ ከመንግስት ባለስልጣናት እና ከተቃዋሚ የፖለቲካ ቡድኖች ጋርም መወያየታቸዉ ተነግሮአል። ጋዜጣዊ መግለጫዉን የተከታተለዉ የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ሃይለ ሚካኤል ይህንን ዘገባ ልኮልናል።
ይልማ ሃይለ ሜካኤል
አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሃመድ