ኢትዮዽያዊው የእግር ኳስ ታላቅ ሰው አረፈ
ዓርብ፣ ታኅሣሥ 8 2003ማስታወቂያ
ሶስተኛውን የአፍሪካ ዋንጫ ኢትዮዽያ እንድታገኝ ያደረገ፤ ለብሄራዊ ቡድን በተሰለፈባቸው 96ግጥሚያዎች በአጠቃላይ 61 ግቦችን ከመረብ ያገናኘ፤ የእግር ኳስ ድንቅ ቴክኒሺያን ነበር መንግስቱ ወርቁ። ቁመቱ አጭር ቢሆንም ከሁለት ሜትር በላይ በመዝለል በጭንቅላቱ ኳስዋን ገጭቶ ጎል የማስቆጠር ብቃቱን ያዩት አሁን ድረስ በአድናቆት ይናገሩለታል። ዛሬ በአዲስ አበባ የቀብር ስነ ስርዓቱ እንደተፈፀመ የአዲስ አበባው ወኪላችን ታደሰ እንግዳው ዘግቧል።
ታደሰ እንግዳው
መሳይ መኮንን
ሂሩት መለሰ