አፍሪቃ፤ የምግብ ችግሯና የፊናንሱ ቀውስ15 ጥር 2001ዓርብ፣ ጥር 15 2001የምግብ ዋጋ በዓለም ገበያ ላይ ባለፉት ዓመታት በተከታታይ እያደገ ነው የመጣው። በአሁኑም ጊዜ ከሰባት አንዱ የዓለም ነዋሪ ለረሃብ የተጋለጠ ነው።https://p.dw.com/p/Gf3Pየምግብ ዋጋ ንረትና የሕዝብ ቁጣምስል APማስታወቂያሆኖም በተለይ በኢንዱስትሪ ልማት የበለጸገውን ዓለም በጠመደው የፊናንስ ቀውስና የኤኮኖሚ ችግር ሳቢያ የታዳጊ አገሮች ሕዝብ መከራ እየተዘነጋ መሄዱ አልቀረም። ጉዳዩ የፊናንሱን ቀውስ ለማሽነፍ የሚደረገው ጥረት አንድ አካል ሆኖ ሊታይ ይገባል፤ የልማት ዕርዳታው መቀነስ ሁሉንም ነው የሚጎዳው የሚል የኤኮኖሚ ባለሙያዎች አስተያየትም አለ።