አፍሪቃ፥ ረሐብና የመሪዎችዋ ዕቅድ
ማክሰኞ፣ ሰኔ 25 2005ማስታወቂያ
የአፍሪቃ ሕዝብን በየአመቱ የሚገድል እና የሚያሠቃየዉን ረሐብን ለማጥፋት የሚረዳ አዲስ ሥልት መየቀየሳቸዉን አዲስ አበባ ዉስጥ ተሰብስበዉ የነበሩት የአፍሪቃ ሐገራት መሪዎች አስታወቁ።ትናንት ተሠብስበዉ የነበሩት የአስራ-አምስት የአፍሪቃ ሐገራት ርዕሳነ-ብሔራትና መራሕያነ-መንግሥታት ባወጡት የጋራ የአቋም መግለጫ የረሐብ ዋናዉ ምክንያት የመርሕ (የፖለሲ) ችግር መሆኑን አምነዋል። መሪዎቹ እንደሚሉት አዲስ በነደፉት ሥልት መሠረት ሚሊዮኖችን የሚያሰቃየዉን ረሐብን እንደ ጎሮጎሮሳዉያኑ አቆጣጠር እስከ 2025 ዓመት ድረስ ከአፍሪቃ ያጠፋሉ። የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ጌታቸዉ ተድላ ሐይለ ጊዮርጊስ ዝር ዝር ዘገባ አለዉ።
ጌታቸዉ ተድላ ሐይለ ጊዮርጊስ
ነጋሽ መሐመድ
ሒሩት መለሠ