አፍሪቃዉያን ስደተኞች በፓሪስ
ሰኞ፣ ግንቦት 3 2007ማስታወቂያ
ሆኖም ግን የሰሞኑ አክራሟ ከወትሮዉ የተለየ መልክ አሰጥቷታል። እንደሃይማኖት ዘገባም ከተማዉን አቋርጦ ከሚሄድ የከተማ ባቡር ድልድይ ሥር የተተለኩት ሰማያዊና አረንጓዴ ትናንሽ ድንኳኖች ለአካባቢዉም ሆነ ለከተማዉ አዲስ ክስተት ሆኗል። በዚህ ስፍራም ቁጥራቸዉ ወደሁለት መቶ የሚጠጉ አብዛኞቹም ከኢትዮጵያ፣ ከኤርትራና ከደቡብ ሱዳን የመጡ ስደተኞች ናቸዉ። ከተሰዳጆቹ ዉስጥም ነፍሰጡሮችና በርካታ ሴቶችም ይገኙበታል። ስደተኞቹን ከፈረንሳይ መንግሥት ምንም ዓይነት ድጋፍ እስካሁን ባለማግኘታቸዉም እዚያ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን በጎ አድራጊዎች ሰብዓዊ እርዳታ እያደረጉላቸዉ ነዉ። ተሰዳጆቹን በስፍራዉ ሄዳ ያነጋገረቻቸዉ ሐይማኖት ከፓሪስ ዝርዝር ዘገባ ልካልናለች።
ሐይማኖት ጥሩነህ
ሸዋዬ ለገሠ
ነጋሽ መሐመድ