1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አጠቃላይ ምርጫ በዴሞክራሲያዊት ኮንጎ

እሑድ፣ ኅዳር 17 2004

በዴሞክራሲያዊት ኮንጎ ሬፑብሊክ በዛሬው ዕለት ፣ እአአ ኅዳር 28፣ 2011ዓም አጠቃላይ ምርጫ እየተካሄደ ነው። ለፕሬዚደንታዊው ምርጫ አስራ አንድ ዕጩዎች፣ ካለፉት አስር ዓመታት ወዲህ ሀገሪቱን በመምራት ላይ ያሉት የአርባ ዓመቱ ፕሬዚደንት ጆሴፍ ካቢላ ጭምር ለውድድር ቀርበዋል።

https://p.dw.com/p/RysH
ምስል AP

ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ዕጩዎች መካከል ለካቢላ ጠንካራ ተፎካካሪ ይሆናሉ የሚባሉት የዴሞክራሲያዊ እና ማህበራዊ ዕድገት ህብረት መሪ ኤትየን ቺሴኬዲ ናቸው። በካቢላ አመራር ስር የሀገሪቱ ኤኮኖሚ ዕድገት ቢያሳይም፡ ሕዝቡ አሁንም ከድህነት አረንቛ አልተላቀቀም። በዚህም የተነሳ የአጠቃላዩ ምርጫ ዘመቻ የብዙውን ሕዝብ ቀልብ የሳበ ሆኖ መቆየቱን ታዛቢዎች ገልጸዋል።

ከፕ/ሽሊንድቫይን

አርያም ተክሌ