1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አዲሷ የተባበሩት መንግስታት ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ከፍተኛ ኮሚሽነር

ማክሰኞ፣ ሐምሌ 22 2000

ደቡብ አፍሪቃዊቷ ዳኛ ናቫንቴን ፒላይ አዲሷ የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር በመሆን ተመርጠዋል ።የአፓርታይድ ስርዓትን ግፍና በደሎች ፣ የዘር መድልዎን

https://p.dw.com/p/Elrx
ኮሚሽነር ፒላይ
ኮሚሽነር ፒላይምስል dpa Zentralbild

እንዲሁም ድህነትን ካሳለፈ ሰራተኛ ቤተሰብ የተወለዱት የስልሳ አራት ዓመቷ ዳኛ ናቫንቴን ፒላይ የሩዋንዳውን የዘር ማጥፋት ወንጀል ለመመልከት የተቋቋመው ዓለም ዓቀፍ ፍርድ ቤት አባል በመሆን ለአራት ዓመታት ሰርተዋል ። በአሁኑ ወቅት ደግሞ በሄጉ ዓለም ዓቀፍ ፍርድ ቤት በዳኝነት በማገልገል ላይ ናቸው ።