1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የባለሥልጣናት መቀየር መፍትሄ ይሆን?

ማክሰኞ፣ የካቲት 20 2010

የባለሥልጣናት ለውጥ አሁን ላሉት የሀገሪቱ መጠነ ሰፊ ችግሮች መፍትሄ እንደማይሆን አንድ የፖለቲካ ጉዳዮች ተንታኝ ተናግረዋል። በመቀሌ ዩኒቨርስቲ የስነ ዜጋ እና ስነ መንግሥት መምህር አቶ ወልደ አብርሃ ንጉሴ እንዳሉት ምናልባት የአዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር መምጣት ለችግሩ ጊዜያዊ ማርገቢያ ከመሆን ውጭ የተሻለ ትርጉም አይኖረውም።

https://p.dw.com/p/2tQKy
Blick aus meinem Fenster Addis Abeba Äthiopien
ምስል Solomon Mengist

አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር ለኢትዮጵያ መፍትሄ ይሆን ይሆን?

 የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የሥራ መልቀቂያ ደብዳቤ ካስገቡበት ጊዜ አንስቶ ማን ይተካቸዋል የሚለው ጥያቄ ማነጋገሩ ቀጥሏል። በዚህ ሳምንት ይካሄዳል ተብሎ በሚጠበቀው በኢህአዴግ ምክር ቤት ስብሰባ የመጪው ጠቅላይ ሚኒስትር ማንነት ይታወቃል የሚል ግምት ነበር። ይሁንና የኢሕአዴግ ስብሰባ ወደ ሌላ ጊዜ መገፋቱ ተነግሯል።ስብሰባዉ ተደረገም አልተደረገ፤ የባለሥልጣናት ለውጥ አሁን ላሉት የሀገሪቱ መጠነ ሰፊ ችግሮች መፍትሄ እንደማይሆን አንድ የፖለቲካ ጉዳዮች ተንታኝ ተናግረዋል። በመቀሌ ዩኒቨርስቲ የስነ ዜጋ እና ስነ መንግሥት መምህር አቶ ወልደ አብርሃ ንጉሴ እንዳሉት ምናልባት የአዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር መምጣት ለችግሩ ጊዜያዊ ማርገቢያ ከመሆን ውጭ የተሻለ ትርጉም አይኖረውም። ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ዝርዝሩን ልኮልናል።  

ዮሐንስ ገብረ እግኢአብሔር

ኂሩት መለሰ

ነጋሽ መሐመድ