አዲስ የስደተኞች ፖሊሲ
ሰኞ፣ ሰኔ 30 2000ማስታወቂያ
የወቅቱ የአዉሮጳ ህብረት ምክር ቤት ሊቀመንበርነትን መንበር የያዘችዉ ፈረንሳይ ህገ ወጥ ፍልሰትን ለመግታት የሚያደርጉትን ጥረትና ሊወሰድ ይገባል የምትለዉን ርምጃ ማጠናከሩን ገፍታበታለች። እንደፈረንሳይ የአዉሮጳ ህብረት አባላት በጥቅሉ አንድወጥ የሆነ የስደተኞች ፖሊሲን ማፅደቅ ይኖርባቸዋል። በደቡባዊ የፈረንሳይ ግዛት የተሰባሰቡት ሚኒስትሮች አሁን የሚደርሱበት ዉሳኔም በመጪዉ ዓመት ጥቅምት ወር የመንግስትና የአገራት መሪዎች በሚሰባሰቡበት ወቅት ይፋ ይሆናል።