አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መምህራን ውይይት
ማክሰኞ፣ መስከረም 17 2009ማስታወቂያ
ባለፈው ሳምንት በሀገር አቀፍ ደረጃ በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች የውይይት እና የምክክር መድረኮች ተካሂደዋል። ከመካከላቸው የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መምህራን እና የአስተዳደር ሠራተኞች ያካሄዱት ውይይት እና ምክክር አንዱ ነው ። በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲው ውይይት የትምህርት ጥራት እና ሌሎች ርዕሶች ለውይይት ቢቀርቡም ፣ የሀገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ ቅድሚያ እንዲሰጠው ተሳታፊዎቹ ባነሱት ጥያቄ መሠረት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውን ተሳታፊዎች ተናግረዋል። ተሳታፊዎቹ እንዳሉት ቀሪው ውይይት በየኮሌጁ እንዲካሄድ በስብሰባው ማጠቃለያ ላይ ተነግሯቸዋል። የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ስለ ውይይቱ ሂደት እና ውጤት የዩኒቨርስቲውን የህዝብ ግንኙነት እና ተሳታፊዎች አነጋግሮ ቀጣዩን ዘገባ አዘጋጅቷል ።
ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ