አዲስ አበባ፤ የኢሕአዴግ ምክር ቤት መግለጫ እየተጠበቀ ነው
ማክሰኞ፣ መጋቢት 18 2010ማስታወቂያ
ወኪሎቻችን እንደገለፁልን በጋዜጣዊዉ መግለጫዉ ላይ ለዉጪ መገናኛ ዘዴዎች የሚዘግቡ ጋዜጠኞች አልተጋበዙም። የኢሕአዴግ ሊቀመንበርነት እና የሐገሪቱ ጠቅላይሚንስትር የነበሩት አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ሥልጣናቸዉን ለመልቀቅ ያቀረቡትን ጥያቄ የግንባሩ ምክር ቤት ዛሬ ማፅደቁን የተለያዩ የሐገር ዉስጥ መገናኛ ዘዴዎች ዘግበዋል። በኢትዮጵያ እስከ ምሽቱ ሁለት ሰዓት ተኩል ድረስ በመገናኛ ብዙሃን የቀረበ ምንም መግለጫ የለም።
ሸዋዬ ለገሠ
ነጋሽ መሐመድ