የአዲስ አበባ ውሎ
ዓርብ፣ ሰኔ 26 2012ማስታወቂያ
ከድምጻዊ ሃጫሉ ግድያ በኋላ እንቅስቃሴዋ ተግቶ የነበረው አዲስ አበባ ዛሬ ወደ ቀድሞው ሁኔታዋ ተመልሳለች ይለናል የአዲስ አበባው ወኪላችን ሰሎሞን ሙጬ ። በከተማዋ አውቶብሶች እና ታክሲዎች የቀድሞ አገልግሎታቸውን እንደቀጠሉ የንግድ እንቅስቃሴዎችም እየተካሄዱ መሆኑን በተለያዩ የከተማዋ ክፍሎችም ተዘዋውሮ መመልከቱንም ተናግሯል።በሌላ በኩል የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ አመራር ወይዘሮ አስቴር ስዩም መታሰራቸውን ባለቤታቸውና ፓርቲያቸው ለዶቼቬለ ተናግረዋል። ትናንት ፍርድ ቤት የቀረቡት የፓርቲው መሪ አቶ እስክንድር ነጋ ደግሞ የጊዜ ቀጠሮ ተስጥቶላቸዋል።
ሰሎሞን ሙጬ
ኂሩት መለሰ