አዲስ አበባ፣ ወንጀለኞች መያዛቸው
ማክሰኞ፣ ግንቦት 6 2011ማስታወቂያ
የአዲስ አበባ ፖሊስ የኢንዶክትሪኔሽንና የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮማንደር ፋሲካ ፋንታ በተለይ ለዶቸ ቬለ DW በስልክ እንደነገሩት ፍተሻዉ ከ10 እስከ 12 ሰዓታት በነበረዉ ጊዜ በአምስት ክፍለ-ከተሞች ድንገት የተደረገ ነበር። በፍተሻዉ ሕገ-ወጥ መድሐኒቶች፤ ሞተር ብስኪሌቶችን ይዟል።ፖሊስ ቀዳሜዉኑ ሌሊቱን ቦሌ ክፍለ-ከተማ በሚገኙ የራቁት ጭፍራ ቤቶች ባደረገዉ አሰሳ አደገኛ ዕፅ፣ ለአደገኛ ዕፅ ሽፋን የሆኑ የሺሻ ማጤሲያዎች፣ አንድ ሽጉጥና 8 ተጠርጣሪ ሰዎችን ይዟል። ኮማንደር ፋሲካ፣ ፖሊስ ከዚሕ ቀደም ባደረገዉ አሰሳና ቁጥጥር የጦር መሳሪዎችንና የጦር መሳሪያ አዘዋዋሪዎችን መያዙን አስታዉሰዋል።ኮማንደር ፋሲካን ነጋሽ መሐመድ አነጋግሯቸዋል።
ነጋሽ መሐመድ
ኂሩት መለሰ