አዲስ ታይምስ መፅሄት መታገዱ
ሰኞ፣ ጥር 27 2005ማስታወቂያ
በየ 2 ሳምንቱ 35 ሺህ ቅጂ ይታተም የነበረው አዲስ ታይምስ መፅሄት መታገዱን የመፅሄቱ ባለቤት አስታወቀ ። የአዲስ ታይምስ ባለቤት ተመስገን ደሳለኝ ዛሬ ለዶቼቬለ እንደተናገረው የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኤጀንሲ 3 ምክንያቶችን ዘርዝሮ መፅሄቱን አግዷል ። አቶ ተመስገን ለእገዳው የተሰጡትን ምክንያቶች መሰረተ ቢስ ሲል አጣጥሏል ። ዶቼቬለ ስለ አዲስ ታይምስ መፅሄት እገዳ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኤጀንሲን አስተያየት ለማግኘት ያደረገው ሙከራ አልተሳካም ። የአዲስ አበባው ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ዝርዝር ዘገባ አዘጋጅቷል ።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ሂሩት መለሰ
ተክሌ የኋላ