1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጦር መሣሪያ ቁጥጥር ረቂቅ አዋጅ 

ረቡዕ፣ የካቲት 6 2011

ረቂቁ እስካሁን ባሉ ህጎች ያልተሸፈኑ የጦር መሣሪያ ቁጥጥርን የተመለከቱ በርካታ ዓለም አቀፍ ሕጎችና ጉዳዮችንም በማካተት ወጥነት ያለው ስርዓት ለመፍጠር ያለመ መሆኑ ተገልጿል። ግለሰቦች የታጠቋቸው የጦር መሣሪያዎች የህብረተሰቡን ሰላም እና ፀጥታ ለማስጠበቅ እንዴት ሊውሉ እንደሚችሉም በረቂቅ ህጉ በዝርዝር መስፈሩም ተነግሯል።

https://p.dw.com/p/3DIbD
Zinabu Tunu, Sprecher der äthiopischen Generalstaatsanwaltschaft in Addis Abeba, Äthiopien
ምስል DW/Solomon Muchie

የጦር መሣሪያ ቁጥጥር ረቂቅ አዋጅ 

የኢትዮጵያ ፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ  አዲስ ያረቀቀዉ  ህገ ወጥ የጦር መሣሪያ ዝውውርን ሊገታ እንደሚችል አስታወቀ። የጠቅላይ አቃቤ ህግ የኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ሃላፊ አቶ ዝናቡ ቱኑ ለDW በሰጡት ቃለ መጠይቅ አዋጁ በአሁኑ ጊዜ ህገ ወጥ የጦር መሣሪያ ዝውውርን ለማስቆም የሚደረገውን ጥረት ይበልጥ ሊያግዝ የሚችል ሁኔታ ይፈጥራል ብለዋል።  

ረቂቁ እስካሁን ባሉ ህጎች ያልተሸፈኑ የጦር መሣሪያ ቁጥጥርን የተመለከቱ በርካታ ዓለም አቀፍ ሕጎችና ጉዳዮችንም በማካተት ወጥነት ያለው ስርዓት ለመፍጠር ያለመ መሆኑንም ገልጸዋል። ግለሰቦች የታጠቋቸው የጦር መሣሪያዎች የህብረተሰቡን ሰላም እና ፀጥታ ለማስጠበቅ እንዴት ሊውሉ እንደሚችሉም በረቂቅ ህጉ በዝርዝር መስፈሩንም ተናግረዋል። አቶ ዝናቡ በቅድሚያ አዋጁን ማዘጋጀት ያስፈለገበትን ምክንያት ያብራራሉ።

ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ