አዲሱ የጀርመን ፕሬዝዳንት
ዓርብ፣ መጋቢት 14 2004ማስታወቂያ
ባለፈዉ እሁድ የተመረጡት የጀርመን ፕሬዝዳት ዩአኺም ጋዉክ ዛሬ ቃለ-መሐላ ፈፅመዉ በይፋ የፕሬዝዳትነቱን ሥራ ጀምረዋል።ፕሬዝዳንቱ ቃለ-መሐላ ከፈፀሙ በሕዋላ ለሁለቱ የሐገሪቱ ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ ባደረጉት ንግግር ጀርመን የሁሉም ዜጎችዋ እኩል ሐገርነቷን ለማስመስከር፥ ቀኝ አክራሪዎችን ለመታገልና ዲሞክራሲያዊ ሥርዓትን ለማጠናከር እንደሚጥሩ አስታዉቀዋል። የጀርመን ፕሬዝዳት ሥልጣን እንደ ርዕሠ-ብሔር ሐገሪቱን ከመወከል ምልክታዊነት ባለፍ ብዙም ወሳኝነት የለዉም።ሥለዚሕ ጉዳይ ቮልፍ ጋንግ ዲክ የዘገበዉን የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ሐይለ ሚካኤል እንደሚከተለዉ አጠናቅሮታል።
ይልማ ሐይለ ሚካኤል
ነጋሽ መሐመድ
ሒሩት መለሰ