አዲሱ የኢትዮጵያ ፓርላማና ካቢኔ
እሑድ፣ መስከረም 30 2008ማስታወቂያ
5 ተኛው የኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባለፈው ሰኞ ሥራውን የጀመረው ከ 20 ዓመታት ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ የተቃዋሚ ፓርቲም ሆነ የግል ተወካይ በሌለበት ነው ። በከዚህ ቀደሞቹ ምክር ቤቶች የተወሰኑም ቢሆኑ ተቃዋሚዎች ና የግል ተመራጮች መኖራቸው ቢያንስ የአንድ ፓርቲ ሃሳብ ብቻ እንዳይሰማ አድርጎ ነበር ። አሁን ግን ፓርላማው ይሄ እድል የለውም ። በ2007 አጠቃላይ ምርጫ የምክር ቤቱን መቀመጫዎች ሙሉ በሙሉ ጠቅሎ የያዘው የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር ኢህአዴግ በሚቀጥሉት 5 ዓመታት ተቆጣጣሪም አስፈፃሚም ሆኖ የሚቀጥልበት አስተዳደር እንዴት ይታያል ? ወዴትስ ሊያመራ ይችላል ? በመጪው እሁድ የሚተላለፈው እንወያይ የመነጋገሪያ ነጥቦች ናቸው ።የውይይቱ ተሳታፊዎች ካነሷቸው ሃሳቦች ውስጥ የሚከተሉት ይገኙበታል ።
ኂሩት መለሰ
እሸቴ በቀለ