አዲሱ የአውሮፓ ህብረት የስደተኞችና የተገን አሰጣጥ ህግ
ዓርብ፣ ነሐሴ 30 2000በአውሮፓውያኑ 2007 ዓመተ ምህረት በአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት ውስጥ ከተያዙት 200,000 ህገ ወጥ ስደተኞች ወደ 90,000 ያህሉ ተገደው ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል ።
የአውሮፓ ህብረት ህገ ወጥ የሚላቸው ስደተኞች ከተያዙ እስከ አስራ ስምንት ወራት ለሚደርስ ጊዜ እንደሚታሰሩ እና ለአምስት ዓመት ያህልም ወደ ተባበሩበት አገር ከመግባት እንደሚታገዱ በአዲሱ ህግ ተደንግጓል ።