1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አውሮፓ ላቲን አሜሪካና የአፍሪቃ ስደተኞች

ማክሰኞ፣ ሰኔ 14 2003

የፖለቲካ ቀውስ ፣ የርስ በርስ ግጭት ፣ ድህነት ስራ አጥነት እና ሌሎችም በርካታ ችግሮች ከተደራረቡበት ከአፍሪቃ ክፍለ ዓለም በየዓመቱ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ስደተኞች በልዩ ልዩ መንገዶች አውሮፓ ለመግባት ይሞክራሉ ።

https://p.dw.com/p/RUyt
ምስል dapd

ይሁንና 27 አገራትን በአባልነት ያቀፈው የአውሮፓ ህብረት ከጊዜ ወደ ጊዜ የድንበር ቁጥጥሩን በማጥበቅ አፍሪቃውያን ስደተኞች አውሮፓ የሚገቡበትን መንገድ እጅግ እያጠበበው ሄዷል ። በዚህም የተነሳ ካለፉት 8 ዓመታት ወዲህ አውሮፓ የሚደርሰው ስደተኛ ቁጥር እየቀነሰ ነው ። ብዙ አፍሪቃውያን አሁን ወደ አውሮፓ ከመሰደድ ይልቅ ወደ ላቲን አሜሪካ ሃገራት መሄዱን መርጠዋል ። ከነዚህም ተመራጭዋ አገር አርጂንቲና ናት ።

ሂሩት መለሰ

ነጋሽ መሐመድ