በአዉሮጳ የሚገደሉና ደብዛቸዉ የሚጣፋ ጋዜጠኞች ጉዳይ
ማክሰኞ፣ መስከረም 29 2011ማስታወቂያ
ጋዜጠኛዋ በምትሰራበት ቴሌቭዥን ከአዉሮጳ ኅብረት በተገኘ ገንዘብ የሚካሄዱ ፕሮጀክቶችን የአፈፃፀም ጉድለት የሚመለከት ዘገባ ከአቀረበች በኋላ መሆኑ ግድያዉን ከስራዋ ጋር አያይዞታል። በአዉሮጳ በተለይ ሙስናን በሚያጋልጡ ጋዜጠኞች ላይ አልፎ አልፎ ግድያ ይፈፀማል። ከአንድ ዓመት በፊት በፓናማዉ የሙስና ቅሌት «የታክስ ማጭበርበር» ጉዳይ ላይ ክትትል ታደርግ የነበረች የማልታ ጋዜጠኛ የነበረችበት ተሽከርካሪ ላይ የተጠመደ ቦንብ መገደልዋ የሚታወስ ነዉ። በሌላ በኩል ቱርክ ዉስጥ ደብዛቸዉ የጠፋዉ የሳዉዲአረብያ ጋዜጠኛም ጉዳይ የሰሞንኛ የመወያያ ርዕስ ሆኖ ነዉ የሰነበተዉ። ጋዜጠኛዉ በሳዉዲ አረብያ ትችት የሚያቀርብ ጋዜጠኛ ነበር። ዝርዝር ዘገባዉን የብረስልሱ ወኪላችን ልኮልናል።
ገበያዉ ንጉሴ
አዜብ ታደሰ
አርያም ተክሌ